በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሱዳን" ተብሎ የሚጠራው ነጭ አውራሪስ ሞተ

በዓለም ላይ በህይወት ያለ ዱር ውስጥ የተወለደ ወንድ የሰሜን ነጭ አውራሪስ ሞተ። የኬንያ የኦል ፔጄታ የዱር አራዊት ጥበቃ መሥሪያ ቤት እንደገለፀው የአርባ አምስት ዓመት ዕድሜ ያለው “ሱዳን” ተብሎ የሚጠራው ነጭ አውራሪስ በዕድሜ ምክንያት የጤናው ይዞታ እየተባባሰ በመመጣቱ ትናንትና እንዲያርፍ ተደርጓል።

በዓለም ላይ በህይወት ያለ ዱር ውስጥ የተወለደ ወንድ የሰሜን ነጭ አውራሪስ ሞተ። የኬንያ የኦል ፔጄታ የዱር አራዊት ጥበቃ መሥሪያ ቤት እንደገለፀው የአርባ አምስት ዓመት ዕድሜ ያለው “ሱዳን” ተብሎ የሚጠራው ነጭ አውራሪስ በዕድሜ ምክንያት የጤናው ይዞታ እየተባባሰ በመመጣቱ ትናንትና እንዲያርፍ ተደርጓል።

በሺሕዎች የተቆጠሩ ጎብኚዎችን ይስብ የነበረው “ሱዳን” ከሁለት በህይወት ከተረፉት ሴት አውራሪሶች ጋር በማገናኘት ዘሩን ጨርሶ ከመጥፋት ለማዳን ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።

ከናይሮቢ ወጣ ብሎ ባለ ስፍራ ከሁለቱ የሱ ዝርያ ከሆኑ ሴት አውራሪሶች ጋር አብሮ እንዲኖር በማድረግ ለማዋለድ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። ባለሙያዎች ወደፊት በሰው ሰራሽ መንገድ ዘሩን ለማባዛት እንዲሞከር የሱን ዘረ መል /ጄኔቲካዊ/ መለዮ ናሙና ወስደው አስቀምጠዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ሳይንቲስቶች ፍቅረኛ ፈላጊዎችን በሚያገናኘው ቲንደር በተባለው የኢንተርኔት መድረክ ላይ “የዓለም ምርጥ ወንደላጤ” በሚል ርዕስ አስቀምጠው ለመዋለድ የሚያስችለው ህክምና የሚጠይቀውን ዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ሞክረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG