ዋሽንግተን ዲሲ —
በሜዳ ቴኒስ እንግሊዛዊው አንዲ ሙራይ እና አሜሪካዊቷ ሴሬና ዊሊያምስ የዊምብለዶን አሸናፊዎች ሆኑ። ሙራይ በዊምብለዶን ነጠላ ግጥሚያ በተደጋጋሚ ሲያሸንፍ ፍሬድ ፔሪ
በ1935 ድል ከተቀዳጀ በሁዋላ የመጀመሪያው እንግሊዛዊ ሆኗል። ሴሬና ዊሊያምስ ግን የዊምብለዶን አሸናፊ ስትሆን ባለፈው ቅዳሜ ለሰባተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።
በአትሌቲክስ በ 5 እና 10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያን ወክለው በሪዮ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ ስምንት አትሌቶች ስም ዝርዝር ይፋ ተደረገ። በሌሎች ርቀቶች የሚሮጡት በቅርቡ እንደሚገለጽ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።