በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የሀገሮች የሃይማኖት ነፃነት ዓመታዊ ሪፖርት


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስ ቴሌርሰን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስ ቴሌርሰን

"በኢራን የባሃይ፥ የክርስትና እና ሌሎች ሕዳጣን ማኅበረሰቦች በዕምነታቸው ሳቢያ ይሳደዳሉ። ኢራን ዕምነትን በመጣል በሚለው የተድበሰበሰ ሕጓ አማካኝነት በዜጎች ላይ የሞት ቅጣት መበየኗን ቀጥላለች።

“በኢራን የባሃይ፥ የክርስትና እና ሌሎች ሕዳጣን ማኅበረሰቦች በዕምነታቸው ሳቢያ ይሳደዳሉ። ኢራን ዕምነትን በመጣል በሚለው የተድበሰበሰ ሕጓ አማካኝነት በዜጎች ላይ የሞት ቅጣት መበየኗን ቀጥላለች።

የሳውዲ መንግሥት የእስልምና ዕምነት ተከታይ ያልሆኑ ዜጎች ዕምነታቸውን በአደባባይ እንዲያሳዩ ካለመፍቀዱም ባሻገር ፈፅመው በተገኙት ላይም የእስር፣ ቅንድብ የመላጨት እና “እምነትን መጣል” .. “ዕምነት አልባ መሆን” .. “ዕምነትን ማዋረድ” እና ‘የመንግሥቱን የእስልምና ሃይማኖት አተረጓጎም መተላለፍ በሚሉ ውንጀላዎች ቅጣት ይበይናል።”

ሬክስ ቴሌርሰን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር።

የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስ ቴሌርሰን በተለያዩ የሃይማኖት ነፃነት መብቶች ጥሰት ይፈፅማሉ፤ ያሏቸውን ሰባት ሀገሮች በስም ጠርተው ተጠያቂ አደረጉ።

ሚ/ር ቴሌርሰን በተጨማሪም “በህዳጣን የማኅበረሰብ አባላትና የሃይማኖት ቡድኖች ላይ የጭካኔ ምግባር ይፈፅማል” ያሉትን እስላማዊውን ፅንፈኛ ቡድን /ISIS/ን ክፉኛ ተችተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ይህን አስተያየታቸውን ያሰሙበትን የትናንቱን የዩኤስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የዓለም አገሮች የሃይማኖት ነፃነት መብቶች ዓመታዊ ሪፖርት ተከትሎ ነው።

ራሱን እስላማዊ ግዛት ብሎ የሚጠራው ፅንፈኛ ቡድን የፈፀማቸውና እየፈፀማቸው ያሉ ዘግናኝ በደሎች በሃይማኖት ነፃነት ላይ ከተደቀኑት አደጋዎች ሁሉ የከፉት ናቸው፤ እንደ ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ዓመታዊ ዘገባ።

ከዓለም ሕዝብ ሰማኒያ በመቶው በዕምነታቸው ላይ በሚጣል አንዳች ገደብና የጥላቻ መንፈስ ተፅዕኖ ሥር በዋለበት፤ በሃይማኖት ሳቢያ የሚደርስ የመሳደድ ጥቃትና ተቀባይነትን የመንፈግ አዝማሚያዎች በሌሎች አካባቢዎችም በእጅጉ እየተስፋፉ መምጣቸውን ቴሌርሰን አመልክተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ዓመታዊ ዘገባ እንደ ሳውዲ አረቢያ የመሳሰሉትን ቁልፍ የዩናይትድ ስቴትስ አጋሮችም ለሁሉም ዜጎቻቸው የሃይማኖት ነፃነትን የሚፈቅድ አሠራር እንዲያራምዱ አሳስቧል።

ቴሌርሰን አክለውም ቱርክን፥ ባሕሬንን፥ ሱዳንን፥ ፓኪስታን እና ቻይናን በስም ጠርተው በሃይማኖት ነፃነት መብቶች በመጣስ ነቅፈዋል።

የሁለት መቶ ሀገሮችን የሃይማኖት ነፃነት መብቶች አያያዝ የሚያጤነውና በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ፍቃድ የተሰጠው ዓመታዊው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሪፖርት በዕምነት ነፃነት ላይ የተደቀነው ፈተና ባልተቋረጠበትም ቢሆን እንደ ቬትናም እና እንደ ተባበሩት የአረብ ኤሜሬቶች በመሳሰሉ አገሮች ሁኔታው በዝግታ እየተሻሻለ ነው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የሀገሮች የሃይማኖት ነፃነት ዓመታዊ ሪፖርት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:09 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG