በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለም ዙሪያ ከ71 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች አሉ - /ዩኤንኤችሲአር/


በዓለም ዙሪያ ጦርነት መሳደድ እና ግጭት አስገድዱዋቸው ከቀያቸው የተፈናቀሉ ቁጥራቸው ከሰባ አንድ ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች መኖራቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር /ዩኤንኤችሲአር/ አስታወቀ።

ይህ አሃዝ /ዩኤንኤችሲአር/ ከሰባ ዓመታት በፊት ከተመሰረተበት ጊዜ ወዲህ ከምንጊዜውም ከፍተኛው መሆኑን አስገንዝቧል።

ድርጅቱ እንደመግለጫው “ሰባ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ተፈናቃይ ያልነው፣ የቬንዙዌላው ቀውስ ያልተካተተበት በመሆኑ ከዚያም ሊበልጥ ይችላል” ይላል፡፡

አራት ሚሊዮን ቬንዙዌላውያን ሃገራቸው ጥለው ተሰደዋል፣ ነገር ግን በይፋ የጥገኝነት ማመልከቻ ያላስገቡ ስለሆኑ በስደተኝነት አልተቆጠሩም ሲል ድርጅቱ አክሏል።

ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት በጦርነትና በተለያዩ ግጭቶች ምክንያት ሃያ ስድስት ሚሊዮን ህዝብ ሃገሩን ጥሎ ተሰዱል፣ ግማሹ ህፃናት ናቸው ብሏል። በተጨማሪም ሌሎች አርባ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ከሀገር ሳይወጡ ከቀያቸው ተሰደዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG