በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፕሬስ ነፃነት ላይ የሚፈጸም ጥቃት በዓለምአቀፍ ህግ ላይ የሚፈጸም ጥቃት ነው


በአዲስ አበባ በተካሄደው የዓለም የነፃነት ቀን አከባበር ላይ ውዝግብ መፈጠሩ ተዘገበ

የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን የላኩት መልዕክት በመክፈቻው ላይ ተሰምቷል። በተወካይ የቀረበው የዋና ጸሐፊው መልዕክት ከስልሳ ዓመታት በፊት የታወጀውን ዓለምአቀፉን የሰብዓዊ መብቶች ውሳኔ የሚያጐላና በተለይም የአንቀጽ ፲፱ኝን መሠረታዊ መብቶች የሚያመለክት ነው። እንዲያውም በፕሬስ ነፃነት ላይ የሚፈጸምን ጥቃት በዓለምአቀፍ ህግ ላይ እንደሚፈጸም ጥቃት ቆጥረውታል።

የአፍሪቃ ህብረት ኰሚሽን ሊቀ መንበር ዶክተር ዣን ፒንግ በበኩላቸው፥ በወከሏቸው የህብረቱ የኰሙኒኬሽን ዲሬክተር አማካይነት በየትም የሚወጡ የፕሬስ ህግጋት የመጀመሪያ የመጨረሻ ግባቸው ምን መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል። «ዘርፉን ሥርዓት ለማስያዝ ያለውን ፍላጐት እንገነዘባለን። ይሁንና የተዘረጉ ሥርዓቶች በምንም መንገድ ለፕሬስ ነፃነት እንቅፋት መሆን እንደሌለባቸው እናምናለን» ሲሉም አስገንዝበዋል።

XS
SM
MD
LG