በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ ዓለማቀፍ ወረርሽኝ ከተባለ አንድ ዓመት ሞላው


የዓለም የጤና ድርጅት ኮቪድ-19ን ዓለማቀፍ ወረርሺኝ ብሎ ካወጀው ድፍን አንድ ዓመት ሞላ።

በዚሁ የወረርሺኙ አንደኛ ዓመት ወቅት የወጣ አንድ አዲስ ጥናት ብሪታንያ ውስጥ የተከሰተው ልውጡ የኮሮናቫይረስ ዓይነት የያዘውን ሰው ከቀደሙት ዝርያዎች ይበልጥ ሊገድል የሚችል መሆኑን አመልክቷል። ጥናቱ በብሪታንያ የህክምና ጆርናል ላይ ታትሟል።

ይህ ጥናት እንደሚያሳየው /B.1.1.7/ የሚባለው ይህ የኮሮናቫይረስ ዝርያ የያዛቸው ሰዎች፣ ከሌሎቹ ዓይነቶች በንጽጽር ከ30% እስከ 100% በሚደርስ መጠን የህልፈት የሚያደርስ አቅም አለው።

የብሪታንያው ልውጥ ኮሮናቫይረስ መጀመሪያ በሃገሪቱ ደቡባዊ ክፍል የተገኘው በመከረም ወር ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከመቶ ወደሚበልጡ ሃገሮች ተዛምቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ የዓለም ሃገሮች ለህዝባቸው የኮቪድ-19 ክትባት ለማዳረስ እየተሯሯጡ ናቸው።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ኩባኒያ ከሚመረተው ክትባት ከተረፈን ለዓለም እናጋራለን ሲሉ ቃል ገብተዋል።

XS
SM
MD
LG