በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም አቀፍ ጉባዔ ስለሊቢያ


የምርጫ ጣቢያ ውስጥ ድምጽ ለመስጠት ምዝገባ ሲካሄድ ሊቢያ፤ ትሪፖሊ
የምርጫ ጣቢያ ውስጥ ድምጽ ለመስጠት ምዝገባ ሲካሄድ ሊቢያ፤ ትሪፖሊ

ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የቆየውን ምርጫ በሚቀጥለው ወር የምታካሂደውን ሊቢያን የተመለከተ ዓለም አቀፍ ጉባዔ ፈረንሳይ በማስተናገድ ላይ ነች።

"ምርጫው በነዳጅ ሃብት በበለጸገችው ሀገር ለአስር ዓመት የዘለቀውን ብጥብጥ ያከትመዋል" ብለው የአካባቢው እና የዓለም ሀገሮች ተስፋ አድርገዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሃሪስን ጨምሮ በርካታ የዓለም መሪዎች በፓሪሱ ጉባዔ ላይ የሚሳተፉ ሲሆን ምርጫው ግልጽ እና ተዓማኒ በሆነ መንገድ እንዲከናወን ግፊት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ጉባዔውን በጋራ በሊቀ መንበርነት የሚመሩት ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ሊቢያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ናቸው።

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሃሪስ ሰኞ ዕለት በሰጡት ቃል በጉባዔው ላይ የሚገኙት ምርጫ ከማካሄድ እየተዘጋጀ ላለው የሊቢያ ህዝብ ያለንን ጠንካራ ድጋፍ ለመግለጽ ነው ብለዋል።

ምርጫው በማይቀለበስና በማያነታርክ መንገድ እንዲከናወን በሊቢያ በኩል የሚካሄደውን የሰው እና የመሳሪያ ህገ ወጥ ዝውውር ለመታገል ወገኖቹ በጋራ ቃል እንዲገቡ የጉባኤው ተካፋዮች ግፊት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ሀገሪቱ የሚገኙት ቅጥር ተዋጊዎች እና ባዕዳን ወታደሮች ለማስወጣት ተጨባጭ ጥረት እንዲደረግም የሚጠይቁ መሆኑን ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑዌል ማክሮን ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሊቢያው የተዋጊዎች መሪ ኻሊፋ ሃፍታር ኃይሎች የጉባዔው አስተናጋጅ ፈረንሳይ ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት ሦስት መቶ ያሉንን ሦስት መቶ ባዕዳን ቅጥር ተዋጊዎች እናስወጣለን ብሏል። መቼ እንደሚያስወጡ የጊዜ ሰሌዳ አላስቀመጡም።

XS
SM
MD
LG