በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮቪድ ወረርሺኝ ምክንያት ህጻናት ህይወት አድን ክትባቶች ሳይከተቡ ቀርተዋል


ይህ ሳምንት የዐለም የክትባት ሳምንት ነው:: በየዐመቱ እአአ በሚያዝያ ወር የመጨረሻ ሳምንት የሚውል ሲሆን የዘንድሮው በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ወቅት መደበኛ ክትባቶቻቸውን ሊከተቡ ያልቻሉ ሰዎች በተለይም ህጻናት ያመለጣቸውን ክትባት እንዲያገኙ ትኩረት የሚሰጥበት እንዲሆን ታቅዷል፡፡

የዘንድሮው የክትባት ሳምንቱ ግብ ተጨማሪ ህጻናትን፡ አዋቂዎችን እና ማህበረሰቦቻቸውን ኩፍኝ እና ፖሊዮን ከመሳሰሉ በክትባት ለመከላከል የሚቻሉ በሽታዎች መጠበቅ መሆኑን የዐለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG