በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም አቀፉ የጤና ጉባኤ በማጠናቀቂያው ዕቅዶችን አጸደቀ


የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም
የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም

ዓለም አቀፍ ወረርሽኞች ሲነሱ ምላሽ የሚሰጥ ስምምነት ለማዘጋጀት የሚያስችል የዓለም ጤና ድርጅት አባል ሀገራት መደራደሪያ እቅድ አፅድቀዋል።

በጄኔቫ ሲካሄድ በቆየው ዓለም አቀፍ የጤና ጉባኤ ሰኞ እለት ሲጠናቀቅ አዲስ ዓለም አቀፍ ስምምነት ወይም በቀጣይ ሊነሱ ለሚችሉ እንደ ኮቪድ-19 ዓይነት ወረርሽኞች ሀገራት የተሻለ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ጉባኤ፣ ልዩ ስብሰባ ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት በህዳር ወር እንዲያካሂድ ድምፅ ሰጥተዋል።

በአሁኑ ወቅት ያለው ወረርሽኝ እ.አ.አ በ2019 ማብቂያ ከተገኘ ጀምሮ በዓለም ዙሪያ ከ170 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ያጠቃ ሲሆን ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ ለተሰብሳቢዎቹ ባደረጉት ንግግር ዓለም አሁን እንደዚህ አይነት ዓለም አቀፍ ስምምነት እንደሚያስፈልጋት ገልፀው፣ የተባበሩት መንግሥታት የጤና ድርጅቶችንና የዓለምን ጤና ደህንነትም እንደሚያጠናክር ገልፀዋል። አክለውም "የመረጃ ፣ የቴክኖሎጂና የግብዓት ልውውጥ አለመኖር" ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተሰጠው ምላሽ ደካማ እንዲሆን እንዳደረገው ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG