በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በድጋሚ ተመረጡ


ፎቶ ፋይል፦ ዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
ፎቶ ፋይል፦ ዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

የዓለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን የድርጅቱ ዳይሬክተር ሆነው ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት እንዲሰሩ በዛሬ እለት በድጋሚ የመረጣቸው መሆኑን በዛሬው እለት አስታውቋል፡፡

እኤአ ከ2017 ጀምሮ የድርጅቱ ዳይሬክተር ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ቴድሮስ ብቸኛው እጩ ሆነው የቀረቡ መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ ቀደም ሲል እኤአ ጥር 2022 ላይ በጤና ድርጅቱ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዕጩ ሆነው በዚህኛው ጉባኤ እንዲቀርቡ መመረጣቸው ተገልጿል፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን የነበሩ ሲሆን በዓለም አቀፉ የኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት ከግንባር የነበረውን ድርጅት የመሩና ድርጅቱ ለወረርሽኙ በሰጣቸው አንዳንድ ምላሾችም ትችት ሲቀርብባቸው የነበረ መሆኑን የአሶሼይትድ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ድርጅቱን በመምራት ከአፍሪካ የመጀመሪያው ሰው መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG