በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ረሃብ እየረገበ ነው


የዓለም የረሃብ ደረጃ ጠቋሚ ካርታ - 2013
የዓለም የረሃብ ደረጃ ጠቋሚ ካርታ - 2013

ጥቅምት 6 የዓለም የምግብ ቀን ነው፡፡
ሆዜ ግራሲያኖ ዳ ሲልቫ - የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብና የግብርና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር /ፎቶ ፋይል/
ሆዜ ግራሲያኖ ዳ ሲልቫ - የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብና የግብርና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር /ፎቶ ፋይል/

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:54 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ጥቅምት 6 / 2006 ዓ.ም የዓለም የምግብ ቀን ነው፡፡

በዓለም ዙሪያ በከበደ ረሃብ ውስጥ ያለው ሰው ቁጥር ባለፈው የአውሮፓዊያን ዓመት ከነበረበት ደረጃ በሰላሣ ሚሊየን ዝቅ ማለቱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና የግብርና ድርጅት - ኤፍኤኦ ዛሬ አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ግን የረሃብተኛው መጠን አሁንም ከስምንት መቶ ሚሊየን በላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ኤርትራ እጅግ አሳሳቢ በሚባል ብርቱ የረሃብ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ሦስት ሃገሮች አንዷ መሆኗን እና ኢትዮጵያ ደግሞ አሳሳቢ የሚባል ረሃብ ካለባቸው 16 ሃገሮች መካከል እንደምትገኝ ከዛሬው የዓለም የምግብ ቀን ጋር ተያይዞ የወጣ የዓለም የረሃብ ደረጃ ጠቋሚ ሠንጠረዥ ያሣያል፡፡

ሃራሬ የሚገኙት የኤፍኤኦ ኃላፊ “በአንድ ወቅት የደቡባዊ አፍሪካ የዳቦ ቅርጫት የነበረችው ዚምባብዌ ወደ ባዶ ቅርጫትነት ተቀይራለች” ብለዋል፡፡ ዚምባብዌ የረሃቡ ሁኔታ “ከባድ ነው” ከሚባልባቸው ሃገሮች አንዷ ነች፡፡

በ2012 ዓ.ም /በአውሮፓ አቆጣጠር/ 870 ሚሊየን ሰው የምግብ እጥረት እንደሚያጋጥመው ተገምቶ የነበረ መሆኑንና በዚህ ዓመት ያ ቁጥር ወደ 840 ሚሊየን መውረዱን የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብና የግብርና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆዜ ግራሲያኖ ዳ ሲልቫ ገልፀዋል፡፡ ይህ ማለት በመላው ዓለም ከስምንት ሰው አንዱ በከበደና ሥር በሰደደ ረሃብ ውስጥ ይገኛል ወይም በየዕለቱ የሚልሰው የሚቀምሰው ነገር የለውም ማለት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
ኤፍኤኦ
ኤፍኤኦ
XS
SM
MD
LG