በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ኢኮኖሚ አዲስ ዝግመት ሥጋት


ዓለምአቀፉ ምጣኔ ኃብት ሌላ የዕድገት ማዝገም ሊገጥመው ይችላል፡፡ የአፍሪቃ ኢኮኖሚ ከተጠበቀው በላይ ያድጋል፤ ሆኖም ከእንቅፋት የፀዳ አይሆንም፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ኢኮኖሚን በቃኘበት ዘገባው ከስድስት ወራት በፊት የሰጠውን ትንበያ ባብዛኛው ሽሮ ግምቱን ዝቅ አድርጎታል።

በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የዓለም ኢኮኖሚ እጅግ አደገ ቢባል በ2012 ዓ.ም በ2.6 በመቶ፣ እና በ2013 ዓ.ም በ3.2 በመቶ ብቻ ይሆናል፡፡ ይህ ማለት ከሁለት ዓመት በፊት 4 በመቶ ከነበረው ይወርዳል ማለት ነው፡፡

ይህ ትንበያ ሊይዝ የሚችለው ደግሞ የዩሮ ቀጣና አገሮች የብድር ቀውስ በቁጥጥር ሥር ከዋለና ባደጉ አገሮች የተያዘው የቀበቶ ማጥበቅ ፖሊሲ ከተገታ ብቻ እንደሆነ ዘገባው ይገልፃል ።

የአፍሪካን ኢኮኖሚ በተመለከተ ግን ዘገባው የተለየ ትንበያ ያለው ይመስላል። አንጻራዊ በሆነ መልኩ ሲታይ ባሳለፍነው ዓመት ማለትም በ2011 ዓ.ም የአፍሪካ አገሮች በተለያየ ደረጃ ይሁን እንጂ የኢኮኖሚ ዕድገት መጠናቸው ጠንካራ ነበር ተብሏል።

ዝርዝሩን ከመለስካቸው አመኃ ዘገባ ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG