በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አስኳሉካን ትሬዲንግ ኩባንያ ብር ወስዶብናል ያሉ ተበዳዮች ሰላማዊ ሠልፍ አደረጉ


አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ላይ ናቸው

አስኳሉካን ትሬዲንግ የተባለ ኩባንያ የዓለም ዕግር ኳስ ዋንጫ ውድድርን ለመከታተል ወደ ደቡብ አፍሪካ ልካችኋለሁ በማለት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ቢሰበስብም ከጉዞውም ከብራችንም ሳንሆን ቀርተናል ያሉ ተበዳዮች ዛሬ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሠልፍ አድረገዋል።

አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገለፀው የፍትህ ሚንስቴርም መንግስት ጉዳዩን እየተከታተለው መሆኑን አስታውቋል።

በቴለቭዥንና በሬዲዮ የተላለፉ ማስታወቂያዎችን ብቻ ሳይሆን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የአቶ ስዩም መስፍንና የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሩን የአቶ ማሃመድ ድሪር ስምና ፊርማ የሰፈረበት ሰነድ ይዘው በመምጣታቸው አምነን እንድንቀበላቸው ምክኒያት ሆኖናል፣ ሲሉ ተበዳዮቹ ያማርራሉ።

ከ97ቱ ምርጫ በኋላ ብዙ የተቃውሞ ሠልፈኞች ባልታዩባት አዲስ አበባ፥ ወደ ሶስት መቶ የሚጠጉት እነኚህ ሠልፈኞች በቂ ትኩረት የሳቡ ይመስላል።

የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG