በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአለም ዋንጫ ሊጀመር አንድ ቀን ብቻ ቀረው


32 ቡድኖች የሚፋለሙበት የአለም ዋንጫ
32 ቡድኖች የሚፋለሙበት የአለም ዋንጫ

ደቡብ አፍሪካ ዝግጅቷን አጠናቃለች

የእግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቁት የአለም ዋንጫ ሊጀመር አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረው። ታላቁን አለም አቀፍ ትይንት ለማዘጋጀት የመጀምሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር የሆነችው ደቡብ አፍሪካም ዝግጅቷን አጠናቃለች። የእግር ኳስ ሜዳዎች አሸብርቀዋል፣ መንገዶች ተፀድተዋል፣ ዘፈኖች ተቀድተው አልቀዋል፣ የደቡብ አፍሪካ ነዋሪዎችም በብዙ ቀለማት ያሸበረቁ ልብሶቻቸውን ለብሰው ወደ መንገድ ወጥተዋል።

እግር ኳስ ተወዳጅና ቁጥር አንድ እስፖርት በሆነባት በሀገራችን ኢትዮጵያም የአለም ዋንጫ ውድድር መጀመር በታላቅ ጉጉት እየተጠበቀ ነው። የአዲስ አበባ ዋና መንገዶች በዚህ አለም ዋንጫ ተሳታፊ በሚሆኑት የእግር ኳስ ቡድኖች ፎቶዎች ተጥለቅልቀዋል። አንድ ወር የሚፈጀው የአለም ዋንጫን ለመከታተል የሚያስችሉ የታተሙ ፕሮግራሞችም በመንገድ እየተሸጡ ነው።

በቪኦኤ ተጠይቀው የነበሩ አንድ አንድ ኳስ ተመልካቾች የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን በሰፊ የሚከታተሉ ቢሆንም፤ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች ከማየት በቀር ብዙዎቻቸው የጨዋታቸው ስልት ማራኪ ስላሃልሆነ ቡድኑን መደገፋቸው አጠራጣሪ እንደሆነ ገልፀዋል። ይልቁንስ ቢሆን ልብ የሚስብ ጨዋታ ይጫወታሉ የሚሏቸውን ሆላንድንና ብራዚልን መደገፍ እንደሚመርጡ ገልፀዋል።

በዚህ የአለም ዋንጫም የአፍሪካ ቡድኖች ጠንክረው መቅረባቸው ተስፋ እንደሰጣቸው በኢትዮጵያ ያሉ ኳስ አፍቃሪያን ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG