በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባራክ ኦባማ በግላስጎ የአየር ንብረት ጉባኤ


የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ
የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ

ስኮትላንድ ግላስጎ ከተማ እየተካሄደ ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ የተሳተፉት መሪዎች ለቀውሱ መፍትሄ ለማምጣት በቂ እርምጃ አልወሰዱም ሲሉ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አሳሰቡ።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ትናንት በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር አብዛኞቹ ሃገሮች እአአ በ2016 በተደረሰው የፓሪሱ የአየር ንብረት ሥምምነት ላይ የገቡዋቸውን ቃሎች አልጠበቁም ብለዋል።

"አብዛኞቹ ሃገሮች በሚገባቸው መጠን ብርታት አላሳዩም፥ ከስድስት አመት በፊት በፓሪሱ ጉባኤ ላይ ተስፋ የተጣለበት ጠንካራ ርምጃ በአንድነት አውን አልሆነም፥ በተለይ ደግሞ ግዙፉን በካይ ጋዝ የሚለቁት ሁለት ሃገሮች የቻይና እና የሩስያ መሪዎች በዚህ ጉባዔ ላይ ለመገኘት እንኩዋን ፈቃደኛ አለመሆናቸው አሳዝኖኛል፥ ይሄን አልደብቃችሁም" ብለዋል የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ።

ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፖን ሀገሮች የመሳሰሉ በኢኮኖሚ እጅግ ያደጉ ሃገሮች በጉዳዩ ዙሪያ መምራት ያለባቸው ቢሆንም ቻይና ህንድ ሩሲያም ይህንኑ እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG