በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሴቶች ኤድስን የሚከላከሉበት ዘዴ መገኘቱ በቪዮናው ጉባዔ ላይ ተገለጸ


በኦስትሪያ መዲና ቪዮና እየተካሄደ ባለው 18ኛው የአለም አቀፍ የኤድስ ጉባዔ ተመራማሪዎች ኤች. አይ. ቪ/ኤድስን በተለይ ሴቶችን በሽታውን ለመከላከል የሚያስችል ቅባት መሰል መድሃኒት መገኘቱ ይፋ ሆኗል።

ግኝቱን የአለም የጤና ድርጅት WHO እና UNAIDS አወድሰው በሴቶች ብልት ላይ የሚቀባው መድሃኒት ሴቶች በበሽታው መያዛቸውን የሚቀንስ መሆኑ ለሴቶች እራስን የመጠበቂያ መንገድ መክፈቱ “ለሴቶች ተስፋ ነው” ብለዋል።

የUNAIDS ስራአስኪያጅ ማይክል ሲዲቤ ቅባቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴቶች እራሳቸውን የሚጠብቁበትን መንገድ የቀየሰ እንደሆነ ተናግረዋል። የአለም የጤና ድርጅት የምርምሩ ውጤት አስተማማኝና የተሳካ መሆኑ ከታወቀ፤ በፍጥነት ለተገልጋዮች የሚደርስበትን መንገድ እንደሚያፈላልግ አስታውቋል።

ቅባቱ ሴቶች ኤች. አይ. ቪ የሚያዙበትን እድል በግማሽ እንደሚቀንስ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG