በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለምርጫው ዝግጅትና የመራጮች አስተያየት


በመጭው ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በንቃት ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ያናገራቸው የሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች ኗሪዎች ገለጹ፡፡

በሌላ በኩል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ በሰቆጣ ምርጫ ክልል ምርጫውን ሰኔ 14 ለማካሄድ ተዘግጅተን ሳለ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ማራዘሙ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበና የመራጩን ህዝብ ስሜት የጎዳ ነው ሲሉ ኗሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

በስድስት አገራዊ ምርጫ ላይ በመራጭነት መሳተፋቸውን የሚናገሩትና በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ የሚኖሩት ሞላ ይመር የዘንድሮው አገራዊ ምርጫ ከቅድመ ዝግጅቲ ጀምሮ አንጻራዊ የዴሞክራሲ ጭላንጭል ታይቶበታል ሲሉ ነበር የገለጹት፡፡

በአካባቢያቸው የነበረውን የቅድመ ምርጫ ዝግጅትና ቅስቀሳ ከሚኖሩበት በደቡብ ወሎ ዞኗ ኮምቦልቻ ከተማ አንጻር የመዘኑት ዘሪቱ አህመድ በበኩላቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎች በነጻነት የተንቀሳቀሱበት እንደሆነ ገልጸዋል፤ በሁለት አገራዊ ምርጫ ላይ የመሳተፍ ተሞክሮ እንዳላቸው በማስታወስ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ስለምርጫው ዝግጅትና የመራጮች አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:00 0:00


XS
SM
MD
LG