በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮሮናቫይረስ የተጠረጠሩ ግለሰብና በጉዞ አብረዋቸው የነበሩ ወደለይቶ ማቆያ መግባታቸው ተገለጸ


የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጤና ፅህፈት ቤት የኮሮናቫይረስ ምልክት የታየበት ግለሰብና ከርሱ ጋር በጉዞ ላይ የነበሩ 36 ሰዎችን ወደ ለይቶ ማቆያ ማስገባቱን አስታወቀ።

በኮሮናቫይረስ የተጠረጠረ ግለሰብን ጨምሮ ከርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች የምርመራ ናሙና ወደ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል የኮሮና ምርመራ ማዕከል ተልኮ ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ የዞኑ ጤና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነገራ ፈይሳ ገልፀዋል።

ወረርሽኙን አስቀድሞ ለመከላከልም በኅብረተሰቡ ዘንድ የሚታየውን መዘናጋት ለማስቀረት የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኮሮናቫይረስ የተጠረጠሩ ግለሰብና በጉዞ አብረዋቸው የነበሩ ወደለይቶ ማቆያ መግባታቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:12 0:00


XS
SM
MD
LG