አዲስ አበባ —
የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ወልቂጤ ከሳምንት በፊት የተጀመረው አድማ እያበቃ ቢሆንም የታሰሩ አለመፈታታቸውን፣ ጥያቄዎችም አለመመለሳቸውን ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ እንኳን የበፊቶቹ ሊፈቱ እኛም እየተፈለግን ነው ብለዋል - ከሦስት ወር በፊት የተቋቋመው የልማት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆነ ወጣት፡፡
የክልሉ መንግሥት በሰጠው ምላሽ የታሰሩት በደረቅ ወንጀል የተሳተፉ ናቸው ብለዋል፡፡ የሞተው ወጣት አንድ መሆኑን በመግለፅም ጉዳዩ እየተጣራ እንደሆነ አስታውቋል - ነዋሪዎቹ የሟቾቹ ቁጥር ሁለት እንደሆነ ነው የሚገልፁት፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ