በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በወልቃት ጠገዴና ጠለምት አካባቢ የወል መቃብሮችን ማግኘቱን ጎንደር ዩኒቨርስቲ ዛሬ አስታወቀ


University of Gondar
University of Gondar

ሪፖርት አቅራቢዎቹ “ህወሓት በወልቃት ጠገዴና በጠለምት አካባቢ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ፈፅሞታል” ያሉትንና “ዘር ማጥፋት” ሲሉ የጠሩትን አድራጎት እንዲያጠና የተላከው የምሑራን ቡድን ሃያ የሚሆኑ የወል መቃብሮችን ማግኘቱን ጎንደር ዩኒቨርስቲ ዛሬ አስታውቋል።

ጥናቱ የሸፈነው ከ1972 ዓ.ም. እስከ 2013 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል። በሌላ በኩል ግን ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ የሚገኘው ህወሓት ትናንት ባወጣው መግለጫ “ራሱን ተበዳይ አድርጎ ለማቅረብ እየሞከረ ነው” ያለውን የአማራ ክልላዊ መንግሥት ከስሶ አስከሬኖቹ በትግራይ ተወላጆች ላይ የተፈፀመ ግድያ ሰለባዎች ናቸው” ብሏል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ደግሞ “እንዲህ ዓይነት ሪፖርት ለማውጣት ሳይንሳዊ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል” ብሏል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

በወልቃት ጠገዴና ጠለምት አካባቢ የወል መቃብሮችን ማግኘቱን ጎንደር ዩኒቨርስቲ ዛሬ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:29 0:00

XS
SM
MD
LG