በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወልድያ ላይ ንብረት የወደመባቸው አቶ ኃይላይ ንጉሤ

ወልድያ
ወልድያ

ወልዲያ ውስጥ የተፈጠረው የከተማዪቱን ማኅበራዊ ስብጥርና ግንኙነቶች የማያንፀባርቅ አሣዛኝ ሁኔታ መሆኑን በሰሞኑ ግርግር የንግድ ተቋማቸውና መኖሪያ ቤታቸው ሙሉ በሙሉ እንደወደሙባቸው የገለፁት የኃይላይ ሕንፃ ባለቤት አቶ ኃይላይ ንጉሤ ለቪኦኤ ገለፁ።

ወልዲያ ውስጥ የተፈጠረው የከተማዪቱን ማኅበራዊ ስብጥርና ግንኙነቶች የማያንፀባርቅ አሣዛኝ ሁኔታ መሆኑን በሰሞኑ ግርግር የንግድ ተቋማቸውና መኖሪያ ቤታቸው ሙሉ በሙሉ እንደወደሙባቸው የገለፁት የኃይላይ ሕንፃ ባለቤት አቶ ኃይላይ ንጉሤ ለቪኦኤ ገለፁ።

ወልድያ ከተማ ውስጥ ከሰላሣ ዓመታት በላይ መኖራቸውን የተናገሩት አቶ ኃይላይ ተዘርፎብኛል ያሉት ቋሚ ያልሆነ ንብረት ግምት ከሦስት ሚሊዮን በላይ እንደሚሆን ተናግረዋል።

ወልድያ ላይ ሰሞኑን የተፈጠረው ችግር መሠረቱ በኳስ ግጥሚያ ምክንያት የተጫረና ለብዙ ውድመት ምክንያት የሆነ የደጋፊዎች አለመግባባት እንደነበረ አስታውሰው በዋናነት በትግራይ ተወላጆች ንብረት፣ የንግድና መኖሪያ ቤቶች ላይ ጥቃት እንደተፈፀመ፣ ነገር ግን የሃገሬውን ጨምሮ አንዳንድ የሌሎችም አካባቢዎች ሰዎች ንብረት ላይ ጉዳት እንደደረሰ አቶ ኃይላይ አመልክተዋል።

አቶ ኃይላይ አምስት ልጆቻቸው ሁሉም የተወለዱት ወልድያ ከተማ ውስጥ እንደሆነ ገልፀዋል።

የአንድ ወዳጃቸውን ልጅ ጨምሮ ሰሞኑን ከተማዪቱ ውስጥ በጠፋው ሕይወት እጅግ እያዘኑ መሆናቸውን አቶ ኃይላይ ተናግረዋል።

ለሙሉው ቃለ ምልልስ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ወልድያ ላይ ንብረት የወደመባቸው አቶ ኃይላይ ንጉሤ
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:28 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG