ዋሺንግተን ዲሲ —
ዊንድ አፕ ራድዮን ያፈለቁት እንግሊዛዊ ተመራማሪ ትሬቨር ባይሊስ በ80 ዓመት እድሜያቸው ትላንት አረፉ።
የሚያውቋቸው ሰዎች እንደሚሉት ከረዥም ጊዜ ህመም በኋላ ነው ያረፉት።
ባይሊስ እአአ በ1990ዎቹ አመታት BayGen ራድዮን ያፈለቁት አፍሪካ ውስጥ የኤድስ በሽታ መስፋፍቱን በቴሌቨዥን ካዩ በኋላ ነው።
የኤሌክትሪክ መብራት በሌለበትና የባትሪ ድንጋይ ለመግዛት አቅም የሌላቸው ሰዎች የህይወት ማዳን መረጃ እንዲያገኙ ለማስቻል ሲሉ ነው ያፈለቁት።
ይህ ግኝታቸው አለም አቀፍ እውቅና 'Obit Trevor Baylis' አትርፎላቸዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ