በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የንግድ ቤታቸው ከካሊፎርኒያው ሰደድ እሳት የተረፈላቸው ኢትዮጵያዊት ኀዘንና ተስፋ


የንግድ ቤታቸው ከካሊፎርኒያው ሰደድ እሳት የተረፈላቸው ኢትዮጵያዊት ኀዘንና ተስፋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:22:25 0:00

የንግድ ቤታቸው ከካሊፎርኒያው ሰደድ እሳት የተረፈላቸው ኢትዮጵያዊት ኀዘንና ተስፋ

በካሊፎርኒያ ግዛት የተስፋፋው ሰደድ እሳት፣ 82 በመቶ የነዋሪዎችን ንብረት ባወደመባት ፓሊሴድስ ውስጥ የሚገኝ "ፓሊሴድስ ዋይን ኤንድ ስፕሪት" የተባለ የዋይን እና ለምግብነት የሚውሉ ቀለል ነገሮች መሸጫ ባለቤቷ ወይዘሮ ተዋበች ፈረደ፣ በአካባቢው ብቸኛ ኢትዮጵያዊት የንግድ ቤት ባለቤት መኾናቸውን ነግረውናል።

ወሮ. ተዋበች፣ አሁን ወደ ስፍራው ተመልሰው ገብተው ለማየት ባይችሉም፣ በአካባቢው በሰደድ እሳቱ ከመቃጠል ተርፏል ከተባለው 18 በመቶ ንብረት ውስጥ የእርሳቸው ንግድ ቤት አንዱ ሊኾን እንደሚችል ተነግሮኛል፤ ይላሉ።

ከሰደድ እሳቱ ነበልባል አምልጠው መውጣታቸውን ቢገልጹም፣ "ለስምንት ዓመት የሠራኹበትና እንደ ቤተሰብ የማያቸው ደንበኞቼ እና ጎረቤቶቼ ንብረት በመውደሙ ግን በቃላት ልገልጸው የማልችለው እጅግ ከባድ ኀዘን ተሰምቶኛል፤" ብለውናል።

በሌላ በኩል እሳቱ በተነሳበት ወቅት በሥራ ላይ የነበሩትና የአስቸኳይ ጊዜ አደጋ ማስጠንቀቂያውን ሰምተው በፍጥነት የደረሱላቸው ባለቤታቸው አቶ ዮሴፍ መቅድም “እዛው እሳቱ ውስጥ ነበርን። የእሳቱ ሙቀት እየተሰማን ነው የወጣነው” ብለውናል።

ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG