የኒዩክሌየር ባለቤት የሆነችው ሰሜን ኮሪያ ትላንት ረቡዕ የሞከረችው የባለስቲክ ሚሳኤል የተተኮሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ከባቡር ላይ በመተኮስ በተካሄደ ሙከራ መሆኑን የአገሪቱ ማዕከላዊ የዜና ወኪል አመለከተ፡፡
ዛሬ ሀሙስ በሳተላይት የተለቀቀው ምስል እንደሚያሳየው ጠቆር ያለ አረንጓዴ ሚሳኤል ማስወንጨፊያ ተራራማ በሆነው አካባቢው ካላ ዋሻ አቅራቢያ ከሚገኝ የባቡር ሀዲድ ላይ ከተጠመደ መሳሪያ ሲተኮስ ታይቷል፡፡
ሙከራው የሰሜን ኮሪያን ተቀንቃሳቅሽ የሚሳኤል ሬጅመንት አቅም በማሳደግ “ብዙ ቦታ የሚገኙ እኩይ ኃይሎችን በአንድ ጊዜ ማደባየት የሚያስችል ኃይል ለመፍጠር ነው” ሲል የአገሪቱ ማዕከላዊ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡
ሰሜን ኮሪያ ይህን የምታደርገው ከዕይታ ውጭ በርካታ ትናንሽ የሚሳኤል መሳሪያዎችን በየቦታው በማሰማራት ለዩናይትድ ስቴትስና ሌሎች ምዕራባውያን አገራት የመከላከሉን እርምጃ አሰቸጋሪ ለማድረግ መሆኑን ተንታኞች ተናግረዋል፡፡
ሰሜን ኮሪያ በትናንትናው እለት ያካሄደቸው የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራው አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑ ይታወሳል፡፡