በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም የሂፐታይተስ ቀን


ፎቶ ፋይል፦ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
ፎቶ ፋይል፦ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

የዓለም የጤና ድርጅ፣ ኮቪድ-19 የሂፐታይትስ ቢ እና ሲ በሽታን በማጥፋት በኩል፣ ተገኝቶ የነበረውን ስኬት፣ እየተፈታተነ ነው ሲል አስጠንቅቋል። ሂፐታይተስ ቢ እና ሲ ጉበት ላይ ጉዳት ከማድረስም በላይ፣ ካንሰር ሊያስከትል ይችላል።

ትናንት የዓለም የሂፐታይተስ ቀን ታስቦ በዋለበት ወቅት፣ የዓለም የጤና ድርጅት ሂፐታይተስ በሽታ፣ ከእናት ወደ ህፃን እንዳይተላለፍ ለማቆም፣ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርቧል።

በዓለም ደረጃ 325 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በሂፐታይተስ ቢ እና ሲ ተይዘዋል። በ 1.3 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች፣ በየዓመቱ በበሽታው እንደሚሞቱ ታውቋል። አስተማማኝ የሆነ የክትባት መድሃኒት በመኖሩ፣ እአአ ከ1980ዎቹ ዓመታት ወዲህ፣ በሂፐታይተስ ቢ የሚያዙ ከአምስት ዓመት ዕድሜ በታች የሆኑ ህፃናት ቁጥር፣ ከአምስት ከመቶ ወደ 1 ከመቶ በታች መውረዱን፣ የዓለም የጤና ድርጂት ጠቁሟል።

ነገር ግን ይህ ስኬት በአንዳንድ የዓለም ሃገሮች፣ በተለይም ከሰሀራ በመለስ ባሉት ሀገሮች፣ በቂ የሂፐታይተስ ቢ ክትባት ስለማይሰጥ፣ በሽታውን ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት እያሰናከለ መሆኑን፣ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አስገንዝበዋል።

በአሁኑ ወቅት የዓለም ትኩረት ኮቪድ-19 ላይ በመሆኑ፣ ሂፐታይትስን ለማጥፍት በሚደረገው ጥረት፣ የተገኘውን ስኬት ሊያሰናከል ይችላል በማለት ዶ/ር ቴድሮስ አሳስበዋል።

XS
SM
MD
LG