ዋሺንግተን ዲሲ —
የቦትስዋ ጋባሮኔ ኮቪድ-19 በአዲስ መልክ በመዛመቱ፣ በድጋሚ ለሁለት ሳምንታት ያህል እንቅስቃሴ አግዳለች። ይህ የሆነው የዓለም የጤና ድርጅት፣ በመላ አፍሪካ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚድረጉ እገዳዎች እንዳይላሉ፣ ባስጠነቀቅበት ወቅት ነው።
አፍርካ ውስጥ የኮሮናቫይረስ መዛመት መጠን፣ ባለፈው ወር በእጥፍ እንደጨመረ፣ የዓለም የጤና ድርጅት ጠቁሟል።
ከ20 በላይ የሚሆኑ የአፍሪካ ሀገሮች፣ ካለፈው ሳምንት የበዙ አዲስ የቫይረሱ በሽተኞች እንደተገኙባቸው መግለፃቸውን፣ በአፍሪካ የዓለም የጤና ድርጅት ቀጠናዊ ሥራ አስኪያጅ ማተሺዲሶ ምየቲ አስገንዝበዋል። ቫይረሱ በብዛት የተዛመተው፣ ደቡብ አፍሪካ ቢሆንም ኬንያ፣ ማዳጋስካር፣ ናይጀርያ፣ ዛምቢያና ዚባብዌ፣ የቫይረሱ መዛመት መጨመሩን ምየቲጠቁመዋል።
ኡጋንዳ፣ ሲሸልስና ሞሪሸስ፣ ቫይረሱን በመቆጣጠር በኩል፣ ጥሩ እየሰሩ መሆናቸውን ምየቲ ግልጸዋል።
እስካሁን ባለው ጊዜ ቫይረሱን በመከላከል ተግባር፣ ስኬት አግኝታ የቆየችው ኩባ፣ ትናንት ዘጠኝ አዲስ የቫይረሱ በሽተኞች ማግኘቷን ገልጻለች። በያዝነው ሳምንት ቀደም ሲል ደግሞ፣ 37 አዲስ በሽተኞች እንዳሉ አስታውቃ ነበር።