በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በፓኪስታን


ፓኪስታን ባለፉት በርካታ ቀናት የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎችዋ ቁጥር ማሻቀቡን ተከትሎ የእንቅስቃሴ እገዳዎቹን እያፈራረቀች ሥራ ላይ እንድታውል የዓለም የጤና ድርጅት አሳሰበ።

ፓኪስታን የቫይረሱ ተያዦች ቁጥር ከ113ሺህ ማለፉን የሞቱትም ከሁለት ሺህ መብለጡን ተናግራለች።

ትናንት የአንድ መቶ አምስት ሰው ህይወት በኮቪድ 19 ሳቢያ እንዳለፈ ታውቋል፤ ይህም አሃዝ እስካሁን በአንድ ቀን ውስጥ ከሞቱት ሁሉ ከፍተኛው እንደሆነ ተገልጿል።

የዓለም የጤና ድርጅቱ የፓኪስታን ተጠሪ ለትልቁ የሀገሪቱ ክፍለ ግዛት ፑንጃብ የጤና ባለሥልጣናት በላኩት ደብዳቤ እንቅስቃሴ እገዳዎቹን በየሁለት ሳምንቱ እያፈራረቁ ሥራ ላይ እንዲያውሉ መክረዋል፤ በቀን ሃምሳ ሺህ ሰው መመርመር መቻል እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በሌላ ዜና በቻይና ኮሮናቫይረስ መጀመሪያ የተቀሰቀሰባት ውሃን ከተማ የሚገኘው ተዘግቶ የከረመው ቆንስላው ሥራ እንደሚጀምር የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ቻይና ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከተማዋን መዝጋትዋን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በጥር ወር የቆንስላውን ሰራተኞችና ቤተሰሰቦቻቸውን ማውጣቱ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG