ዋሺንግተን ዲሲ —
የዓለም የጤና ድርጅት በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በሕዝብ ላይ በብሄራዊ ደረጃ ሊያደርስ የሚችለውን አደጋ አስመልክቶ የደረሰበትን ግምገማ “ከከፍተኛ ወደ በጣም ከፍተኛ” አሳድጎታል።
በአካባቢ ደረጃ የሥጋቱ መጠን መካከለኛ - በዓለም ደረጃ ሲታይ ደግሞ አነስተኛ መሆኑንም የዓለም የጤና ድርጅት በሪፖርቱ ጨምሮ ገልጿል።
የዓለም የጤና ድርጅት ይህን ሪፖርት ለማውጣት የተገደደው ከሦስቱ “የባንዳካ” የጤና ዞኖች ባንደኛው - አዲስ በኢቦላ ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች መገኘታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ነው። በሰሜን ምዕራብ ክፍለ ሃገር በኢኳተር ከተማ “በባንዳካ“ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ይኖራል።
የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ ሁኔታውን “አሳሳቢ” ሲሉ ገልፀውታል።
በዓለሙ የጤና ድርጅት ገለፃ መሠረት የኢቦላ ቫይረስ ተከስቷል ወደተባለበት ከተማ ቕኝት የሚያካሂዱ 30 ባለሞያዎችን ልኳል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ