በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤድስ ሥጋት እንደገና እያንሠራራ ነው


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ከፀረ-ኤችአይቪ/ኤድስ መድኃኒቶች ጋር የተለማመደው የቫይረስ ዓይነት የኤድስን ሥጋት ይበልጥ እያባባሰው መምጣቱን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል።

ከፀረ-ኤችአይቪ/ኤድስ መድኃኒቶች ጋር የተለማመደው የቫይረስ ዓይነት የኤድስን ሥጋት ይበልጥ እያባባሰው መምጣቱን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል።

ድርጅቱ ማስጠንቀቂያውን ያወጣው በአሥራ አንድ ሃገሮች ላይ የተካሄደን ጥናት ውጤት መሠረት አድርጎ ነው።

በዓለም ዙሪያ ዛሬ ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ የሚገኝ ሰው ቁጥር 36.7 ሚሊየን ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆነው ፀረ-ኤችአይቪ/ኤድስ መድኃኒት ይወስዳል።

በአሥራ አንድ የአፍሪካ፣ የእሥያና የላቲን አሜሪካ ሃገሮች ውስጥ የተካሄደው ጥናት እንደሚያሣየው በስድስቱ ውስጥ ካሉ የመድኃኒት ተጠቃሚዎች አሥር ከመቶ የሚሆኑት መድኃኒቱን ከተለማመደና አልበገር እያለ ከመጣ ቫይረስ ጋር ነው እየታገሉ ያሉት።

ከዓለም አጠቃላይ የኤችአይቪ ሥርጭት ከሁለት ሦስተኛው በላይ የሚገኝበት ከሠሃራ በስተደቡብ ያለው ክልል ሲሆን ኤችአይቪ መድኃኒቱን እየተለማመደ የሚገኘው የመድኃኒቱ አቅርቦትም በተመናመነባቸው አካባቢዎች መሆኑን በዓለም የጤና ድርጅት የኤችአይቪ ሕክምናና እንክብካቤ መርኃግብር አስተባባሪ ሜግ ዶኸርቲ ለቪኦኤ አመልክተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኤድስ ሥጋት እንደገና እያንሠራራ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:25 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG