በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሮናቫይረስ መዛመት መባባሱን የዓለም የጤና ድርጅት ጠቆመ


ፎቶ ፋይል፦ የዓለምቀፍ የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም
ፎቶ ፋይል፦ የዓለምቀፍ የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም

በዓለም ዙሪያ የኮቪድ-19 ተጋላጮች ቁጥር ከሃምሳ አምስት ሚሊዮን ባለፈበት እና ታመው ለህልፈት የተዳረጉት ከአንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን በሆነበት ባሁኑ ወቅት የቫይረሱን መዛመት መቆጣጠሩን ቸል የሚሉ ሃገሮች በእሳት እየተጫወቱ ነው ሲሉ የዓለምቀፍ የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም አሳሰቡ።

ዶ/ር ቴድሮስ ትናንት በጄንኔቫ የድርጅቱ ዋና ጽህፈት ቤት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የኮሮናቫይረስ መዛመት እየተባባሰ መሆኑ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ለቫይረሱ ከተጋለጠ ሰው ጋር የነበራቸውን ንክኪ ተከትሎ ለሁለት ሳምንት ራሳቸውን አግልለው ቆይተው የነበረ ሲሆን ከዚያ ወዲህ የትናንቱ የመጀመሪያ ጋዜጣዊ ጉባኤአቸው ነው፤

የዩናይትድ ስቴትሱ የመድሃኒት ኩባኒያ ሞደርና የሰራው የኮሮናቫይረስ ክትባት ዘጠና አምስት ከመቶ ውጤታማነት የማሳየቱ ዜና የሚያስደስት መሆኑን የገለጹት የዓለሙ የጤና ድርጅት ሥራ አስኪያጁ ሆኖም የቫይረሱን መዛመት ለመግታት እርምጃ የማይወስዱት ሃገሮች በእሳት እየተጫወቱ ናቸው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ከሞደርና በፊት ፋይዘር እና የጀርመኑ ባዮኤንቴክ ኩባኒያ የሰሩት ክትባት እየተካሄደ ባለው ሙከራ ተመሳሳይ ውጤት እንዳስገኘ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ፋይዘር እና ባዮኤንቴክ የሰሩት ክትባት እጅግ ቀዝቃዛ በሆነ ማቀዝቀዣ መቀመጥ ያለበት በመሆኑ ማጓጓዝና ማከፋፈል ላይ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ከወዲሁ ስጋታቸውን እየገለጹ ናቸው።

XS
SM
MD
LG