በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በኢትዮጵያ ያለው የጤና ቀውስ አሳስቦኛል" - የዓለም ጤና ድርጅት


 የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም

በኢትዮጵያ እየተባባሰ ያለው የጤና ችግር፣ ድርቅ፣ ግጭት እና የሰዎች መፈናቀል በሽታንና ረሃብን እያባባሰ መጥቷል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አሳሰበ።

ከ80 በላይ ቋንቋዎች ተናጋሪ የሆኑ ማኅረሰቦች ባሉባትና በአፍሪካ በሕዝቧ ብዛት ሁለተኛዋ በሆነችው ሃገር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ‘በዘውግ ማንነት እና በግዛት ይገባኛል’ ጥያቄ የተነሳ ግድያዎችን ያስከተሉ ጥቃቶች ማጋጠማቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

‘በጥቅምት 2016 በሰሜን ኢትዮጵያ በመንግሥት ኃይሎች እና አማጽያን መካከል የተካሄደው ጦርነት የጅምላ ፍጅት ማስከተሉን ያወሳው ዘገባ ከሁለት ዓመታት በኋላ በጥቅምት 2016 የተደረሰውን "ግጭቶችን የማቆም" ሥምምነት ተከትሎ በጊዜው በአካባቢው ይካሄድ ነበረው ጦርነት ቢያበቃም፣ በሌሎች አካባቢዎች የሚካሄዱትን ግጭቶች ግን አላስቆመም። የዚያች አገር መከራም አላበቃም’ ብሏል።

በትግራይ እና በአማራ ክልሎች የሚታየው ድርቅ ወደ ቸነፈር መቃረቡን የሚገልጹ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችን ጨምሮ ግጭቶች፣ ድርቅ እና መፈናቀል የከፋ ረሃብና ወረርሽኝ እያስከተሉ ነው"

የዓለሙ የጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ትናንት ረቡዕ ጄኔቫ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፡ ‘በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች እየተባባሰ የመጣው ቀውስ ድርጅታቸውን በእጅጉ እንዳሳሰበው አመልክተው "በትግራይ እና በአማራ ክልሎች የሚታየው ድርቅ ወደ ቸነፈር መቃረቡን የሚገልጹ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችን ጨምሮ ግጭቶች፣ ድርቅ እና መፈናቀል የከፋ ረሃብና ወረርሽኝ እያስከተሉ ነው" ብለዋል።

የኤልኒኞ የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለው ድርቅ በመላው ኢትዮጵያ ከ17 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለጉዳት መዳረጉን ተቁመው፡ በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ያሳደረው ተፅዕኖ ግን አሳሳቢ መሆኑን ዶ/ር ቴድሮስ አድኀኖም ተናግረዋል። አክለውም "በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት፣ ድርቅ፣ የኢኮኖሚ ቀውስ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በተለይም በትግራይና በአማራ ክልሎች የበሽታ ወረርሽኝ እየተስፋፋ ነው" ብለዋል።

"የወባ፣ የኩፍኝ፣ እና የደንጊ በሽታዎች እየተበራከቱ ይገኛሉ" ያሉት የዓለሙ ጤና ድርጅት ድሬክተር የሚያስፈልገውን እገዛ መጠን እና ዓይነት ለመገምገም ወደ ተጎዱ አካባቢዎች የበለጠ ተደራሽነት እንዲደረግ ጠይቀዋል። በአማራ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን አመልክተው፤ ከቦታ ወደ ቦታ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መገ’ደብ የሰብአዊ ረድዔት አቅርቦትን ማስተጓጎሉንም ጨምረው ገልጠዋል።

የዓለሙ ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋዎች ክፍል ድሬክተር ማይክል ራያን በበኩላቸው ድርጅታቸው በቀውስ የተጠመዱ አንዳንድ አገሮች ቀደም ሲል ከተከሰቱ ፈተናዎች ሊያገግሙ ከማይችሉባቸው የቀውሶች አዙሪት ውስጥ ወድቀው እያየ መሆኑን ተናግረዋል። "እንዳለመታደል ሆኖ እያየን ያለነው ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ተለያዩ ተደጋጋሚ ቀውሶች የሚሸጋገሩ፣ ግጭት እና የተጋላጭነት አዘቅት ውስጥ የሚወድቁ ሀገራት ስብስብ ነው" ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG