በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢቦላ በኡጋንዳ መዲና ካምፓላ እየተዛመተ ነው


ፎቶ ፋይል፦ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
ፎቶ ፋይል፦ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

የኢቦላ ወረርሽን ወደ ኡጋንዳ መዲና ካምፓላ መድረሱ፣ የገዳዩ በሽታ ወደፊት በስፋት የመሰራጨቱን አደገኛነት ያሳያል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ትናንት አስጠንቅቋል። አገራት በሽታውን ለመከላከል ያሚያደርጉትን ዝግጅት እንዲያጠናክሩም ጥሪ አድርጓል።

ባለፈው መስከረም ወረርሽኑ መከሰቱን የኡጋንዳ ጤና ሚኒስቴር ካስታወቀ በኋላ 150 ሰዎች በበሽታው ሲያዙ፣ 60 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል ሲል የጤና ድርጅቱ ጨምሮ አስታውቋል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ተውሳኩ ባለፈው ሳምንት ካምፓላ ከገባ በኋላ 17 ሰዎች መያዛቸው ተረጋግጧል።

በመዲናዋ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎችና የኡጋንዳ ጎረቤት በሆኑት አገሮች ዝግጅት እንደሚያስፈልግም ጨምረው መክረዋል።

ኢቦላ ከሰውነት በሚወጣ ፈሳሽ አማካኝነት የሚተላለፍ ሲሆን፤ ትኩሳት፣ትውከት፣ ተቅማጥና ሌሎች ምልክቶች ሲኖሩት፣ መከላከል የሚቻለው በአብዛኛው በሽታው የያዛቸውን ሰዎች በመለየት ነው።

በኡጋንዳ ለተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ከዚህ በፊት የጤና ድርጅቱ ከመደበው 5 ሚሊዮን ዶላር በተጨማሪ፣ ባለፈው ማክሰኞ 5.7 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍ መደረጉን የዐለም የጤና ድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጨምረው ማስታወቃቸውን የኤ.ኤፍ.ፒ ዘገባ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG