በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የክትባቱን ግብ የማያሳካው ፖለቲካና ትርፍ ነው” ዶ/ር ቴድሮስ


ፎቶ ፋይል፦ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም
ፎቶ ፋይል፦ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም የኮቪድ-19 “ወረርሽኙ የሚቆመው ዓለም እንዲቆም ሲፈልግ ብቻ ነው” ሲሉ ትናንት እሁድ በሰጡት መግለጫ ተናገሩ፡፡

ጀርመን ላይ በተካሄደ የዓለም የጤና ጉባኤ ላይ የተናገሩት ድሬክተሩ “አገሮች አሁን ያሉትን መሳሪያዎች ሁሉ ተጠቅመው ወረርሽኙን የማይታገሉ ከሆነ፣ ወረርሽኙ የሚቆምበትም ምንም መንገድ የለም” ብለዋል፡፡

ቴድሮስ ከ100 አገራት በድረ ገጽ ላይ ለተሰባሰቡ ታዳሚዎች፣ ባሰሙት ንግግራቸው “በሽታዎችን ለመቋቋም የሚያስችሉን ሁሉንም ዓይነት መሳሪያዎች አሉን፟፣ ውጤታማ የሆኑ የጤና መሳሪያዎች፣ ውጤታማ የሆኑ የህክምና መሳሪያዎች ፡ ዓለም ግን እነዚህን መሳሪያዎች እየተጠቀመ አይደለም፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት፣ እያንዳንዱ አገር 40 ከመቶ የሚሆኑ ዜጎችን ለማስከተብ ያስቀመጠውን ግብ እንዳያሳካ ያደረገው “ትርፍና ፖለቲካ” እንጂ “የምርት ጉዳይ አለመሆኑን” የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ከዜጎቻቸው 40 ከመቶውን ማስተከብ የቻሉ በተለይ የቡድን 20 አገሮችን ጨምሮ በየበለጸጉ አገሮች በኮቫክስ አማካይነት ድርሻቸው ለሌሎች የአፍሪካና የድሆች አገሮች እንዲያዋጡ ቴድሮስ አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG