በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ 19 ለዓለም አስጊ የጤና ችግር መሆኑ አብቅቷል - የዓለም ጤና ድርጅት


የኮቪድ ክትባት
የኮቪድ ክትባት

ኮቪድ 19 በአደገኛ ወረርሽኝ ደረጃ መታየቱና ለዓለም አስጊ የጤና ችግር ተደርጎ መታየቱ አብቅቷል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ትናንት አስታውቋል።

ዜናው 6.9 ሚሊዮን ሕይወት የቀጠፈውንና የዓለምን ኢኮኖሚን ያናጋውን ወረርሽኝ ወደ ማቆም ለሚደረገው ጉዙ ትልቅ ተስፋ ነው ተብሏል።

የጤና ድርጅቱ በጥር 2012 ወረርሽኙን በአደገኛ ደረጃ መድቦ፣ ከዛ በኋላም የድርጅቱ ባለሙያች ቡድን በየሦስት ወሩ እየተሰበሰበ ያንኑ ደረጃ ሲሰጥ ቆይቷል።

የባለሙያዎቹ ቡድን ትናንት ባደረገው ስብሰባ ወረርሽኙ ለዓለም አስጊ የጤና ችግር መሆኑ አብቅቷል ብሏል።

XS
SM
MD
LG