በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ ለ14.9 ሚሊዮን ሰዎች ሞት ምክንያት ነው አለ


የዓለም ጤና ድርጅት ድሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም
የዓለም ጤና ድርጅት ድሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም

የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 እኤአ ከጥር 1/2020 አንስቶ እስከ ታህሳስ 31/2021 ድረስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመላው ዓለም ለ14.9 ሚሊዮን ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን አስታወቀ፡፡

የተጠቀሰው ቁጥር ተጨማሪ ሞት ተብሎ የሚጠራውን የሚመልከት ሲሆን በኮቪድ የሞቱትና ከኮቪድ ውጭ ሊሞቱ የሚችሉ ሰዎችን በማስተያየት መሆኑን የጤና ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

የተቋሙዋና ድሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ባወጡት መግለጫ ዓለም አቀፉ ድርጅቱ ከሁሉም አገሮች ጋር አብሮ በመስራትን የጤና መረጃ ልውውጥና ሥር ዓታቸውን ለተሻለ ውሳኔና ለተሻለ ውጤት እንዲያግዝ ለማጠንክር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዓለምአቀፉ የጤና ድርጅት ከሞቱ ሰዎች ውስጥ 84 ከመቶ የሚሆኑት በደቡብ ምስራቅ እስያ አውርፓና አሜርካስ ተብለው በሚጠሩት ክፍለ ዓለሞች መሆኑን አስታውቋል፡፡

በወረርሽኙ ከሞቱት ውስጥ 57 ከመቶ የሆነው የወንዶች ቁጥር ከፍተኛው ሲሆን የሴቶች 47 ከመቶ መሆኑን የጤና ድርጅቱ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG