በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“እያሻቀበ የመጣውን የኮሌራ ሕሙማን ብዛት ለመዋጋት አጣዳፊ እርምጃ ያስፈልጋል” የዓለም የጤና ድርጅት


የኮሌራ ክትባት በኩዌዛና ፖሊ ክሊኒክ እየተሰጠ ሃራሬ፣ ዚምባብዌ እአአ ጥር 29/2024
የኮሌራ ክትባት በኩዌዛና ፖሊ ክሊኒክ እየተሰጠ ሃራሬ፣ ዚምባብዌ እአአ ጥር 29/2024

በዓለም ዙሪያ በኮሌራ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን በዚያም ላይ የክትባት እጥረት እንዳለ የገለጸው የዓለም የጤና ድርጅት አስቸኳይ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት አሳሰበ፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት የክትባት አቅርቦት ጉዳዮች ዓለም አቀፍ አስተባባሪ ተቋም ትናንት ረቡዕ ባወጣው መግለጫ የኮሌራ ሕሙማን ቁጥር ካሁን ቀደም ባልነበረ መልኩ ለተከታታይ ዓመታት እያሻቀበ በመሆኑ ሁኔታውን ለመቆጣጠር አጣዳፊ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ሲል አሳስቧል፡፡

ባሁኑ ወቅት የሚያስፈልገውን የኮሌራ ክትባት ለመሟላት እጅግ የከበደ የክትባቱ እጥረት እንዳለ መግለጫው ጨምሮ አስታውቋል፡፡ በመላው ዓለም ያለውን የክትባት መጠን የሚቆጣጠረው ቡድኑ እጥረቱ ቢያንስ ለቀጣዮቹ ዓመታት እንደሚቀጥል ተናግሯል፡፡

የዓለሙ የጤና ድርጅት አካል የበሽታውን ስርጭት መባባስ ለመቆጣጠር እንዲወሰዱ ከጠየቃቸው እርምጃዎች መካከል የንጹሕ ውሃ አቅርቦት እንዲሻሻል የአካባቢ ጽዳት እና የግል ንጽሕና አገልግሎቶችን ማጠናከር የሚሉት ይገኙበታል፡፡

የኮሌራ መከላከያ ክትባት የሚያመርተው ብቸኛው ኩባኒያ የደቡብ ኮሪያው ኢዩ ባዮሎጂክ (EU BIOLOGIC) ባሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ በሚያስፈልገው የክትባት መጠን ሊያመርት እንደማይችል ተመልክቷል፡፡

እአአ በ 2022 ዓም የዐለም የጤና ድርጅቱ ተቋም የነበረውን የክትባት እጥረት ለመቋቋም በሚል በሁለት ጊዜ ምጥን ይሰጥ የነበረውን ክትባት አንድ ጊዜ ብቻ እንዲሰጥ ምክር ሃሳብ አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG