በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዲሬክተር ለጋዛ የአስቸኳይ ሰብአዊ ተኩስ አቁም ጥሪ አቀረቡ


ፎቶ ፋይል፦ የዓለም ጤና ድርጅት(WHO) ዋና ዲሬክተር ዶር. ቴድሮስ አድኀኖም
ፎቶ ፋይል፦ የዓለም ጤና ድርጅት(WHO) ዋና ዲሬክተር ዶር. ቴድሮስ አድኀኖም

የዓለም ጤና ድርጅት(WHO) ዋና ዲሬክተር ዶር. ቴድሮስ አድኀኖም፣ የምግብ፣ የሕክምና ቁሳቁስ እና ሌሎች ርዳታዎች፣ ወደ ጋዛ ሰርጥ ለማድረስ ይችል ዘንድ፣ አስቸኳይ የሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ።

ዶር. ቴድሮስ፣ በኢትዮጵያ፣ በጦርነት ውስጥ ያደጉበትን የመከራ ጊዜ ገጠመኛቸውን በማስታወስ፣ ‘ኤክስ’ ተብሎ በሚጠራው የቀድሞው ትዊተር የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ እያሰሙ ያሉት “የተኩስ አቁም ተማፅኖ እና የሰላም ጥሪ” እንደኾነ አመልክተዋል።

“በልጅነቱ በጦርነት ጥላ ውስጥ እንዳደገ ሰው፥ ድምፁን፣ ጠረኑንና ገጽታውን በቅርበት አውቀዋለኹ፤” ያሉት ዶር ቴድሮስ፣ አያይዘውም፣ “በአሁኑ ወቅት፣ በግጭቱ አጣብቂኝ ውስጥ ለሚገኙት ሰዎች በእጅጉ አዝናለኹ፤ ሕመማቸውም የራሴ ያህል ኾኖ ይሰማኛል፤” ብለዋል።

"ጦርነት የሚያመጣው ውድመት፣ ሽብር እና ጥፋት ብቻ ነው። የሚያስገኘው አንዳችም ረብ የለም፤” ሲሉም አክለዋል።

“ልጆቹን እንዳየኹ፣ ከ50 ዓመታት በፊት የነበረ ኹኔታ ነው ወደ አእምሮዬ የመጣው። ግልጽ ብሎ የሚታይና የሚያውክ፣ የጦርነት ሽታ፣ የጦርነት ድምፅ እና የጦርነት ምስል ነው፤” ሲሉ፣ እንባ እየተናነቃቸው ተናግረዋል። “ያ ነው፣ በማንም ላይ እንዲደርስ የማልፈልገው። ስለኾነም፣ ሰላም ይመጣል ብዬ ተስፋ አደርጋለኹ፤” ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG