በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዋይት ኃውስ የኢድ አልፈጥርን በዓል ያከብራል


 የዩናይትድ ስቴትት ፕሬዚዳን ጆ ባይደን እና ባለቤታቸው ጂል ባይደን
የዩናይትድ ስቴትት ፕሬዚዳን ጆ ባይደን እና ባለቤታቸው ጂል ባይደን

የዩናይትድ ስቴትት ፕሬዚዳን ጆ ባይደን የሙስሊሞች ቅዱስ ሮሞዳን ፆም ያበቃበትን የኢድ አልፈጥር በዓል ለማክበር የእምነቱ ተከታዮችን የጋበዙበት ዝግጅት በዋይት ኃውስ ማሰናዳታቸው ተነገረ፡፡

በዋይት ኃውሱ ዝግጅት ላይ ፕሬዚዳንቱ፣ ባለቤታቸው ጂል ባይደን፣ እና የምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኽሪስ ባለቤት ዳግ ኢምሆፍን እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

ባይደንና ባለቤታቸው ትናንት እሁድ ምሽት ባወጡት መግለጫ “የሃይማኖት ነጻነት ለሁሉም የሚለው ልማድ አገራችችን ያጠነክራል፣ ስለሆነም ይህንን ሰር የሰደደ መሠረታዊ የወል መርሃችንን ለማጠንከር የተለያዩ እምነት ተከታዮችና የማኅበረሰብ ክፍሎች አባላት ከሆኑት ሁሉም አሜሪካውያን ጋር መስራታችንን እንቀጥላለን፡” ብለዋል፡፡

አስከትለውም “በመላው አገራችን የበለጠ መረዳትና ህብረትን ለመፍጠር የሚስሩ ሙስሊም አሜሪካውያንን ለማክበርና ለማነቃቃት፣ በዚህ ዓመት በዋይት ኃውስ ይክበር የነበረውን የኢድ በዓል ልማድ በድጋሚ እንጀምራለን” ብለዋል፡፡

ያለፈው ዓመት የዋይት ኃውስ የኢድ በዓል በኮሪናቫይረስ ምክንያት የተካሄደው በድረ-ገጽ መሆኑን ታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG