በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ፑቲንን ለሁለተኛ ጉባዔ ዋሺንግተን ጋበዟቸው


ፎቶ ፋይል፡- የሩስያ ፕሬዚዳንት ቪላዲሚር ፑቲን
ፎቶ ፋይል፡- የሩስያ ፕሬዚዳንት ቪላዲሚር ፑቲን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ የሩስያው ፕሬዚዳንት ቪላዲሚር ፑቲንን ሁለተኛ ጉባዔ ለማካሄድ ዋሺንግተንን እንዲጎበኙ ጋበዟዋቸው።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ የሩስያው ፕሬዚዳንት ቪላዲሚር ፑቲንን ሁለተኛ ጉባዔ ለማካሄድ ዋሺንግተንን እንዲጎበኙ ጋበዟዋቸው።

ዩናያትድ ስቴትስና ሩስያ የመሪዎቻቸውን ጉባዔ ዝግጅት በተመለከተ እየተነጋገሩ መሆናቸውን የዋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ሣራ ሃከቢ ሳንደርስ ትናንት በማኅበራዊ መገናኛ አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ የብሄራዊ ፀጥታ አማካሪያቸው ጆን ቦልተንን የፕሬዚዳንት ፑቲን እንዲመጡ እንዲጋብዟቸው ጠይቀዋል፡፡ በዚያ ዙሪያ ንግግሩ ተጀምሯል ሲሉ ሣራ ሃከቢ በትዊተር አስታውቀዋል።

የብሄራዊ ደኅንነት ዳይሬክተሩ ዳን ኮትስ ኮሎራዶ ውስጥ በተከሄደ ጉባዔ ላይ ፑቲን በወራት ውስጥ ዋሺንግተንን ሊጎበኙ እንደሚችሉ ሲነገራቸው “ሊከሰት ስለሚችለው የደኅንነት ሥጋት ገምግመን ፕሬዚዳንቱ እንዲያውቁት እናደርጋለን ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG