በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዋይት ሃውስ በአባይና በኅዳሴ ግድብ ላይ መግለጫ አወጣ


ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት
ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት

ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት በአባይና በኅዳሴ ግድብ ላይ ማምሻውን መግለጫ አውጥቷል።

የኢትዮጵያን ታላቁን ኅዳሴ ግድብ ለመሙላትና አገልግሎቱንም ለማስኬድ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የትብብር፣ ዘላቂነት ያለውና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያመጣ ስምምነት ላይ ለመድረስ በግብፅ፣ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል እየተካሄዱ ያሉትን ድርድሮች እንደምትደግፍ ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቀች።

ከዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት የፕሬስ ኃላፊ ማምሻውን የወጣው አጭር መግለጫ ”ሁሉም የአባይ ተፋሰስ ሃገሮች የምጣኔኃብትና የብልፅግና መብት አላቸው” ይላል።

በመቀጠልም “እነዚያን መብቶች የሚጠብቅና በተመሣሣይ ጊዜም በአባይ ውኃ ላይ የሁሉንም የውኃ ድርሻ እኩልነት የሚያከብር ስምምነት ላይ እንዲደርሱ የሚያስችል ቀና ጥረት እንዲያደርጉ አስተዳደሩ ለሁሉም ወገኖች ጥሪ ያደርጋል” ብሏል።

መግለጫው የወጣበት ምክንያት አልተገለፀም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG