የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በዚህ ሣምንት ውስጥ የተከለሰ የጉዞ ዕገዳ ትዕዛዝ ያወጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
በሌላ በኩል ግን የሃገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት የመኖሪያ ሠነድ የሌላቸውን ሰዎች በኃይል እየያዙ ከሃገር ማስወጣትን የሚያሰፋና የኢሚግሬሽን መመሪያዎችን የሚያጠብቅ አዲስ መመሪያ አውጥቷል፡፡
ከሃገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት የወጣው አዲስ ማስታወሻ የኢሚንሬሽን ደንቦችን ለማስፈፀም ይበልጥ ጠንካራ የሆኑ እርምጃዎችን እንደሚወስድ የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ሾን ስፓይሰር ዛሬ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ