በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድ የዕቃ መጫኛ መኪና ከዋይት ሃውስ አጥር ጋር ተጋጨ

አንድ የቤት ዕቃ መጫኛ መኪና ትናንት ማምሻውን በዋይት ሃውስ አጠገብ ያለን የደህንነት አጥር ጥሶ ለማለፍ ሲሞክር ተጋጭቶ መያዙን የፕሬዚዳንቱ ጥበቃ ኃይል፣ ሲክረት ሰርቪስ አስታውቋል።

የመኪናው የኋላ ዕቃ መጫኛ በር በሮቦት ተከፍቶ፣ በውስጡ ፈንጂም ሆነ ሌላ አድገኛ ነገር እንደሌለው ፖሊስ አረጋግጧል። የናዚ ስዋስቲካ ባንዲራ ከመኪናው ውስጥ እንደተገኘ ተዘግቧል።

የሚዙሪ ግዛት ነዋሪ የሆነው የ 19 ዓመቱ ወጣት፣ ሳይ ቫርሺት ካንዱላ መኪናውን ሆን ብሉ ከደህንነት አጥሩ ጋር ሳያጋጭ እንዳልቀረ የፕሬዚዳንቱ ጥበቃ ኃይል ገልጿል። ክስ ይመሠረትበታልም ተብሏል።

ከዋይት ሃውስ አቅራቢያ የሚገኘው የሄይ አዳምስ ሆቴል እንግዶች ለደህንነታቸው ሲባል እንዲወጡ መደረጉም ታውቋል።

ግለሰቡ፣ ፕሬዚዳንቱ እና ምክትል ፕሬዝደንቱ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው ላይ አደጋ ለማድረስ ወይም ሕይወት ለማጥፋት እንዲሁም ለመጥለፍ በመሞከር የሚሉ ክሶች ሊመሠረትበት እንደሚችል በመነገር ላይ ነው።

XS
SM
MD
LG