በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን በእሥራኤል በተያዘው ጎላን ሀይትስ የሮኬት ጥቃቶች መክፈቷ ተወገዘ


የዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥት ኢራን በእሥራኤል በተያዘው ጎላን ሀይትስ የሮኬት ጥቃቶች መክፈቷ አውግዟል። “ተቀባይነት የሌለውና ለመላ መካከለኛው ምሥራቅ እጅግ አደገኛ ክስተት ነው” ብሎታል።

የዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥት ኢራን በእሥራኤል በተያዘው ጎላን ሀይትስ የሮኬት ጥቃቶች መክፈቷ አውግዟል።

“ተቀባይነት የሌለውና ለመላ መካከለኛው ምሥራቅ እጅግ አደገኛ ክስተት ነው” ብሎታል።

የዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥት ዛሬ ማለዳ ባወጣው መግለጫ “የኢራን እሥላማዊ የአብዮት ጥበቃ ጓድ ኃላፊነት ለጎደለው ተግባሩ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ይሆናል።” ካለ በኋላ የአብዮት ጥበቃውና ተወካዮቹ ተጨማሪ “ተንኳሽ እርምጃ” ያለውን እንዳይወዱ አስጥንቅቋል።

እሥራኤል በበኩሏ ሌሊቱን ሦርያ ውስጥ ያሉትን በርካታ የኢራን ወታደራዊ ዒላማዎችን በመምታት ምላሽ መስጠትዋን ዛሬ ገልፃለች።

የእሥራኤል ወታደራዊ ኃይል የአየር ድብደባ በሥለላ ቦታዎች፣ በጦር መሳርያ ማከማቻና በሎጂስቲካ ማዕከሎች ያተኮረ ነበር ይላል። ተዋጊ ጄቶቹ በርካታ የሦርያን የአየር መከላከያ ሥርዓትን ደምስሰዋል ሲሊም አክሏል።

የኢራን አደጋ ሦርያ ውስጥ ሥር እንዲሰድ እንደማይፈቅና የሦርያ መንግሥት በግዛቱ ለሚፈፀም ሁሉ ተጠያቂ ይሆናል ሲል አስጠንቅቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG