በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ኦባማኬር” እንዲሠረዝ ዋይት ሃውስ ‘አቤት’ አለ


በምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ የኮቪድ-19 ምላሽ ግብረኃይል በሁለት ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ መግለጫ ይሰጣል።

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት


በሀገሪቱ ኮሮናቫይረስ ከምንጊዜውም በተስፋፋ ሁኔታ እየተዛመተ መሆኑ እየተነገረ ባለበት ባሁኑ ወቅት “ኦባማኬር” እየተባለ በተቀጥላ ስሙ የሚታወቀው ለዓቅም ተመጣጣኝ የጤና ዋስትና ድንጋጌ እንዲሠረዝ ዋይት ሃውስ ትናንት ለዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ አስገብቷል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሠራተኞች የጤና ዋስትና የሚያገኙት በሚሠሩበት መሥሪያ ቤት ወይም ድርጅት በኩል ሲሆን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሠራተኞች ሥራቸውንም የጤና ዋስትናቸውንም አጥተዋል።

ከዚያም በተጨማሪ የጤና ዋስትና የማይሰጡ አሠሪዎች ስላሉ ሠራተኛው በግሉ ለመግዛት የሚገደድ ሲሆን የ“ኦባማኬር” ሕግ የወጣውም ሰዉ በዐቅም ተመጣጣኝ የጤና ዋስትና መግዛት እንዲችል ታስቦ ነበር።

የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፐሎሲ “በዚህ የኮቪድ-19 ቀውስ መሃል ሰዉን የጤና ዋስትና ለመንጠቅ ዘመቻ መክፈታቸው ምን ዓይነት ክፋት እንደሆን ሊገባኝ እይችልም” ሲሉ አውግዘዋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር የፊታችን ጥቅምት ሊያዳምጥ ቀጠሮ ይዟል።

XS
SM
MD
LG