በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከ5 እስከ 11 ዓመት ዕድሜ ያሉ ልጆችን ለመከተብ ዕቅድ ተሰናዳ


ፎቶ ፋይል:-የመጀመሪያ የትምህርት ቀን አንድ ሕፃን የፊት ጭንብል ለብሶ ወደ ትምህር ቤት ሲያመራ፣ በብሩክሊን ፣ ኒው ዮርክ።
ፎቶ ፋይል:-የመጀመሪያ የትምህርት ቀን አንድ ሕፃን የፊት ጭንብል ለብሶ ወደ ትምህር ቤት ሲያመራ፣ በብሩክሊን ፣ ኒው ዮርክ።

በፋይዘር ለተሰራው የኮቪድ-19 ክትባት ለልጆች እንዲሰጥ በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት ፈቃድ ካገኘ በኋላ ከአምስት እስከ አስራ አንድ ዓመት የሆኑ ልጆች በሙሉ የሚከተቡበትን ዕቅድ አሰናድተናል ሲል ኋይት ሐውስ በዛሬው ዕለት አስታወቀ።

የኋይት ሐውስ የኮሮናቫይረስ አስተባባሩ ጄፍ ዜንትስ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ክትባቶቹ ህፃናትን ለጉዳት እንደማይዳርጉ እርገጠኛ ለመሆን እንዲሁም በቂ ክትባቶችም እንዲዘጋጁ ለማድረግ የባይደን አስተዳደር ባለፉት በርካታ ሳምንታት ከክፍለ ሀገር እና ከከተሞች አስተዳደሮች ጋር ሆኖ ሲሰራ መቆየቱን አስረድተዋል።

ክትባቶቹ ለህጻናት ሃኪሞች ልጆችን ለመክተብ በሚቀልል መንገድ ትናንሽ መርፊዎችን ማቅረብን ጨምሮ እንዲዘጋጁ ፋይዘር ሲሰራበት መቆየቱን ዚየንትስ አመልክተዋል።

ኋይት ሐውስ ክትባቶቹን በማከፋፈል ለመርዳት በሀገሪቱ ዙሪያ ሃያ አምስት ሺህ የህጻናት ልዩ ሃኪሞች የቤተሰብ ጤና ዶክተሮች የህጻናት ሆስፒታሎች፣ የመድሃኒት ቤቶች እና የማኅበረሰብ የጤና ጣቢያዎችን መመዝገቡን ባለሥልጣኑ አብራርተዋል።

ልጆች ክትባቱን እንዲከተቡ ከተፈቀደ ወይም ሲፈቀድ ቤተሰቦች በተዛባ መረጃ ምክንያት “ልጆቻንን አናስከትብም” እንዳይሉ አስቀድሞ መከላከል አስፈላጊ መሆኑን ዋናው የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ጤና ጥበቃ ባለሥልጣን ሰርጀን ጄኔራል ቪቬክ ሙርቲ አሳስበዋል።

ይህን ለማድረግ ተዓማኒ ሃኪሞች እና የጤና ኤክስፐርቶች እርዳታ ያስፈልጋል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG