በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ስንዴ ምርትና የባለሙያዎች አስተያየት


የኢትዮጵያ ስንዴ ምርትና የባለሙያዎች አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:55 0:00

የኢትዮጵያ ስንዴ ምርትና የባለሙያዎች አስተያየት

ኢትዮጵያ የስንዴ ፍላጎቷን በአገር ውስጥ ምርት ከመሸፈን አልፋ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ሰፊ የመኸር እና የመስኖ ልማት እያካሄደች ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ ቅድመ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን እያስታወቀች ነው፡፡

ቪኦኤ ያነጋገራቸው ሁለት የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ዶ/ር ጉቱ ቴሶ እና ዶ/ር ፈቃደ ገላው ግን ዘገባው የተጋነነ፣ ከሁኔታዎች ጋር ያልተገናዘበና የኢትዮጵያን የምግብ እጥረት ችግር የማይፈታ መሆኑን ይናገራሉ።

“ኢትዮጵያ ልትልክ የምትችለው የስንዴ መጠን ምን ያህል ይሆናል? ምን ያህልስ ገቢ ሊያስገኝ ይችላል? አዋጭነቱስ ምን ያህል ነው?” ሲሉም ባለሙያዎቹ ይጠይቃሉ፡፡

“ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን ብትችል በምግብ ራሷን ቻለች ማለት አይደለም” ሲሉም ይከራከራሉ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ስንዴን ወደ ውጭ መላክ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ከስንዴ ላኪ ባለሀብቶች ጋር ጥቅምት 29/2015 ውይይት ማድረጉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወደ ውጭ የሚላከው ስንዴ ከአገር ውስጥ ፍጆታ የተፈረ መሆኑን ሚኒስትሩ አቶ ገ/መስቀል ጫላ ባላፈው መስከረም 6/2015ዓም መናገራቸውም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያ ከሠሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮ ትልቁ የስንዴ አምራች አገር ብትሆንም አሁን ድረስ ስንዴን ከውጭ አገር የምታስመጣ መሆንዋ ይነገራል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ "በተያዘው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ስንዴን ለውጪ ሀገር ገበያ ለማቅረብ ወደ ያዝነው ግብ ቀርበናል" ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG