በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዋትስአፕ የኢንተርኔት ቀበኞችን መቆጣጠሪያ ዘዴውን አጠበቀ


የዋትስአፕ አርማ /ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ/
የዋትስአፕ አርማ /ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ/

“ከባለ አድራሻው ውጭ ማንም የመልዕክቱን ይዘት ማወቅ ወይም ማየት አይችልም። የትኛውም የኢንተርኔት ቀበኛ ወይም ቀማኛ፤ አለያም ጨካኝ መንግስታት፤ ማንም ምንም ማድረግ ሆነ ምንም ማግኘት አይቻለውም። እኛ ራሳችን እንኳን ያለ ባለቤቱ ፈቃድ መልዕክቱን ማወቅ ወይም ማየት አንችልም።” ጃን ኮም የዋትስአፕ(WhatsApp) ዋና ሥራ አስፈጻሚ።

ዝነኛው የፈጣን መልዕክት መላላኪያ ዋትስአፕ (WhatsApp) የተጠቃሚዎቹን መረጃ ሚስጢራዊነት ለማረጋገጥ መልዕክቶች በሚስጥር የሚተላለፉበት አዲስ መላ አስተዋወቀ።

ከባለ አድራሻው ውጭ ማንም የመልዕክቱን ይዘት ማወቅ ወይም ማየት አይችልም። የትኛውም የኢንተርኔት ቀበኛ ወይም ቀማኛ፤ አለያም ጨካኝ መንግስታት፤ ማንም ምንም ማድረግ ሆነ ምንም ማግኘት አይቻለውም። እኛ ራሳችን እንኳን ያለ ባለቤቱ ፈቃድ መልዕክቱን ማወቅ ወይም ማየት አንችልም።
ጃን ኮም የዋትስአፕ(WhatsApp) ዋና ሥራ አስፈጻሚ

የፈጣኑ የማሕበራዊ መገናኛ ብዙኃን መላላኪያ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጃን ኮምይፋ ያደረጉት የኢንተርኔት ጽሁፍ ተገልጋዮች በግልም ሆነ በቡድን የሚለዋወጧቸው መልዕክቶች ምስጢራዊነት ከመነሻው እስከ መድረሻው የሚረጋገጥበት ቴክኖሎጂ መሆኑን አመልክቷል።

“ዋትስአፕ” ይፋ ያደረገው የዚህ እርምጃ ዜና የተሰማው በኢንተርኔት አማካኝነት በግለሰቦች ጥብቅ መረጃዎች ላይ የሚፈጸሙ ዘረፋዎች፤ የደህንነት ዋስትናዎች አደጋ ላይ መውደቅ በሥፋት እያነጋገገረ ባለበት ባሁኑ ወቅት ነው።

በግለሰቦች መረጃ አይደፈሬ ምስጢራዊነት መረጋገጥና ብሔራዊ ደህንነትን በማስጠበቅ (መንግስታዊ) ኃላፊነት መካከል ያለውን ሚዛን መጠበቅ አስመልክቶ ዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ትኩረት የተሰጠው ክርክር በማስተናገድ ላይ ያለችበት ወቅትም ነው።

ዝርዝሩን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

ዋትስአፕ የኢንተርኔት ቀበኞችን መቆጣጠሪያ ዘዴውን አጠበቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG