በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በአፍሪካ ያላትን መሠረት እያጠናከረች ነው


የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ

የሩሲያ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሰርጌ ላቭሮቭ ሩሲያ በአፍሪካ ያላትን ተጽእኖ ለማስፋት፣ በጊኒ፣ በኮንጎ ሪፐብሊክ፣ በቡርኪናፋሶ እና በቻድ በዚህ ሳምንት ተዘዋውረው ባደረጉት ጉብኝት ለሀገራቱ እርዳታ እና ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

ሩሲያ ነባሮቹን እንደ ፈረንሳይ እና አሜሪካ ያሉትን ሀገራት በመተካት ለብዙ የአፍሪካ ሀገራት ተመራጭ የደህንነት አጋር እየሆነች ነው።

ሞስኮ የአፍሪካ መሪዎች ደህንነትን ለመጠበቅ እና ጽንፈኞችን የመዋጋት የሚያደርጉትን ጥረት ለመርዳት፣ እንደ ዋግነር እና ተተኪውን አፍሪካ ኮርፕስን የመሰሉ የግል የደህንነት ኩባንያዎችን ትጠቀማለች።

ሩሲያ በበኩሏ የዩክሬንን ወረራ በተመለከተ ከ54ቱ የአፍሪካ ሀገራት የፖለቲካ ድጋፍ ወይም ቢያንስ ገለልተኝነትን ትሻለች፡፡ በተባበሩት መንግስታት ውስጥ ትልቁን የደምጽ ሰጭዎች ወገን እንደያዙ የሚነገርላቸው የአፍሪካ ሀገራት፣ የሩሲያን ወራራ በመተቸቱ ረገድ በጣም የተለያየ የአቋም ልዩነት እንዳላቸው ተመልክቷል።

ከሩሲያ ጋር የተገናኙ አካላት አፍሪካውያን ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማፍረስ የሀሰት መረጃዎችን እያሰራጩ ነው የሚል ክስ የሚቀርብ ሲሆን፣ “ሞስኮ ከ22 በላይ በሆኑ ሀገራት ላይ ያነጣጠሩ፣ 80 በሰነድ የተረጋገጡ ዘመቻዎችን ታካሂዳለች” ሲል አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ሩሲያ መንፈንቅለ መንግስት በሚዘወተርባቸው በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች ያሉትን የፖለቲካ አለመረጋጋቶችና ተቃውሞዎችን፣ እንዲሁም የቀድሞ ቅኝ ገዥ በሆነችው ፈረንሳይ ላይ ያለውን ተቃውሞና ቁጣ እንደ ጥሩ አጋጣሚ እየተጠቀመችበት መሆኑንም ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።

ፈረንሣይ እና አሜሪካ በሳህል አካባቢ ያለውን አክራሪነት ለመዋጋት ቢጥሩም፣ ብጥብጥና አለመረጋጋቱ ጨምሯል፣ ይህም ወደ ቁጣ እና ሩሲያን ወደ መደገፍ እንዲሸጋገር ማድረጉ ተገልጿል።

በሳህል አካባቢ ከአልቃይዳና እስላማዊ መንግስት ቡድኖች ጋር የተቆራኙ አክራሪዎች እንቅስቃሴ ባለፉት ዓመታት እየተጠናከረ መምጣቱም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG