በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከደቡብ አፍሪካ ጋር ልምምድ የሚያደርጉት የሩሲያ እና የቻይና መርከቦች ደርሰዋል


ከደቡብ አፍሪካ ጋር ልምምድ የሚያደርጉት የሩሲያ እና የቻይና መርከቦች ደርሰዋል
ከደቡብ አፍሪካ ጋር ልምምድ የሚያደርጉት የሩሲያ እና የቻይና መርከቦች ደርሰዋል

በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት የባህር ኃይል ልምምድ የሚያደርጉት የሩሲያ እና የቻይና መርከቦች ትናንት ሰኞ ደቡብ አፍሪካ ሪቻርድ ቤይ ባህረ ሰላጤ ገብተዋል።

በዩክሬን ጦርነት እና ቻይና ራስ ገዟን ታይዋንን በሚመለከት የምትከተለው ፖሊስ ይበልጡን እየከረረ ባለበት በዚህ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ውጥረቶች እየተጋጋሉ መሆኑን ያወሳው የሮይተርስ ዘገባ በመሆኑም የዓለም ኃያላን አፍሪካ ውስጥ ተጽዕኖእቸውን ለማሳደር እየተፎካከሩ መሆናቸውን አመልክቷል።

ደቡብ አፍሪካ ከሩስያ እና ከቻይና ጋር የምታደርገው የባህር ኃይል ልምምድ መደበኛ ልምምድ መሆኑን ትናገራለች። ይሁን እንጂ ሮይተርስ ያነጋገራቸው ደቡብ አፍሪካ ያሉ የስድስት የኔቶ እና አውሮፓ ህብረት አባል ሀገሮች ዲፕሎማቶች የጦር ልምምዱን አውግዘዋል።

ዩክሬንን በሚመለከት ገለልተኛ አቋም እንደምትከተል የምትናገረው ደቡብ አፍሪካ ባለፈው ዓመት ሩስያን ባወገዘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውሳኔ ድምጸ ተአቅቦ ማድረጓ ይታወሳል።

ተንታኞች በበኩላቸው ደቡብ አፍሪካ ለአስር ቀን የሚቆይ የጦር ልምምድ ለዚያውም ሩሲያ ዩክሬንን የወረረችበት አንደኛ ዓመት በሚታሰብበት በዚህ ወቅት ማስተናገዷ አደገኛ ጉዳይ እንደሆነ ይናገራሉ።

XS
SM
MD
LG