ዋሺንግተን ዲሲ —
የብዙሃን ድምጽ የሚወከልበት ነውና እስከ ዛሬ ከሚታወቁት ዓይነተኛ የመንግሥት አስተዳደር ሥርዓቶች ሁሉ ተመራጩ ነው።
ያ የብዙሃን ድምጽ እስከተሰማም ድረስ ታዲያ … አንዳንዴ የምንፈልገውን ብቻ ሳይሆን፤ የማንፈልገውን ጭምር ሊሰጠን የሚችለው ይህ ዘመን የጠገበ የአስተዳደር ሥርዓት ዘይቤ ሌላ የዘመን ፈተናዎችም የገጠሙት ይመስላል።
ለመሆኑ ለምን ይሆን (ድፍን ዓለም ማለት ይቻላል) ዲሞክራሲን ከሁሉ ተመራጭ ስርዓት ያደረገበት ምስጢር?
በዓለም በተሻለ የመንግሥት አስተዳደር ዘይቤነቱ የሚዘከረውን ዲሞክራሲን “ዲሞክራሲ” የሚያሰኙትስ መሠረታዊ ነገሮች ምንድ ናቸው? የፍልስፍና እና የፖለቲካ ሳይንስ ንድፈ ሃሳቦችን ያጣመረውን ዓለም የሚመራበትን ዘመናት የዘለቀ ሥርዓት ምንነት መለስ ብለን እንደ አዲስ መልከት እናደርጋለን።
ሙሉ ዘገባውን ከዚህ ያድምጡ።